ዓባይ ባንክና ዳሽን ቢራ አ.ማ. ሠራተኞች ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክና ዳሽን ቢራ አ.ማ. ሠራተኞች ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16/2014- ዓባይ ባንክ ለዳሽን ቢራ አ.ማ. ሠራተኞች የቤት እና መኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የዳሽን ቢራ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ማሪዮ ቫን ገርደር በተገኙበት በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በማስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ አገልግሎቶችን እያቀረበ ሲሆን÷ ቀደም ሲል ለተለያዩ ድርጅቶች ሠራተኞች የብድር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስምምነት በማድረግ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ዋግ ልማት ማህበር፣ ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል፣ ኑር ኢንተርናሽናል፣ አይኤፍ ዓለምአቀፍ የማዳበሪያ ልማት ማዕከል እና ሌሎችም ድርጅቶች ሰራተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡   

Leave a Reply

Your email address will not be published.