ዓባይ ባንክ ለባሕር ዳር መሰናዶ ትምህር ቤት ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ ለባሕር ዳር መሰናዶ ትምህር ቤት ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ አ.ማ በባሕር ዳር መሰናዶ ትምህርት ቤት የሴት ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ውሃ ማጣሪያ ግንባታ አሰርቶ ለትምህርት ቤቱ አስረከበ፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የባንኩ የባሕር ዳር ቀጠና ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ጸጋዬ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ስራዎችን በስፋት እየሰራ መሆኑን አንስተው÷ በባሕር ዳር መሰናዶ ትምህርት ቤት የተደረገውም ግንባታ የዚሁ አካል መሆኑን በመግለጽ ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

ግንባታውን ዓባይ ባንክ እና ስፕላሽ ኢንተርናሽናል የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋራ በመሆን ያከናወኑት ሲሆን÷ ደረጃውን የጠበቀ መጸዳጃ ቤት፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ውሃ ማጣሪያ መገንባቱ ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እንደሚያግዝ አቶ ሲሳይ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ዓባይ ባንክ ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት ለተለያዩ ተቋማትንና የማህበረሰብ ክፍሎች ትርጉም ያለው ድጋፍ በማድረግ ኃፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን÷ በቅርቡም የባንኩ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ደም መለገሳቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.