ዓባይ ባንክ ለዋግ ልማት ማሕበር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ ለዋግ ልማት ማሕበር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 05/ 2014 – ዓባይ ባንክ አ.ማ ለዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) የሶስት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ባንኩ ድጋፉን ያደረገው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከሰቶ በነበረው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ እና በዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በተለያዩ አካባቢዎች ሥር ለሚገኙ ከ75ሺህ   በላይ ተፈናቃይ ወገኖች፣ ከለጋሽ ድርጅቶች የተገኙትን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ወደቦታው ለማድረስ የተጠየቀውን ወጪ ለመሸፈን የሚውል ነው፡፡

ባንኩ በልማት ማህበሩ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በመገኘት ድጋፉን ማድረጉ ታውቋል፡፡

ዓባይ ባንክ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን፣ በቅርቡም የባንኩ ሠራተኞች በሰሜን ወሎ ዋግህምራ እና ሰቆጣ አካባቢዎች በድርቅና ረሀብ ለተጎዱ ወገኖች አራት ሚሊየን ብር የሚገመት የስንዴ ዱቄት መለገሳቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.