ዓባይ ባንክ ለፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ ለፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ብር 360,000.00 ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን አቶ አቡበከር ነዚር የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠባባቂ ምክትል ዋና መኮንን ለዶ/ር አሚን መሐመድ አሊ የሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ በክፍለ ከተማው በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ አስረክበዋል፡፡

ድጋፉ የክፍለ ከተማው እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለሚያከናውናቸው ዘርፈብዙ ሥራዎች እንደሚውል ታውቋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ከክፍለ ከተማው የተውጣጡ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት የተገኙ ሲሆን፣ ባንኩ የሚሰጣቸውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶች በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ዓባይ ባንክ እና የሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ባንኩ በሚሰጠው ሰዲቅ – ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.