ዓባይ ባንክ በባህርዳር ከተማ የደንበኞች ውይይት አደረገ

ዓባይ ባንክ በባህርዳር ከተማ የደንበኞች ውይይት አደረገ

ዓባይ ባንክ በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር አገልግሎት አሰጣጥ እና አጠቃላይ የባንኩን ሥራ አፈጻጸም በተመለከተ ውጤታማ ውይይት በአቫንቲ ሆቴል አከናውኗል፡፡

በውይይቱ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ ባንኩ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ደንበኞች ከባንኩ ጋር አብረው በመስራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን÷ በቀጣይም ባንኩ በተለየ መልኩ የደንበኞች ፍላጎትን የሚመጥኑ አገልግሎቶችን እንዲሁም ቀልጣፋና ፈጣን የደንበኞች አገልግሎት እንደሚያቀርብ ቃል ገብተዋል፡፡

ደንበኞች በበኩላቸው ባንኩ የደንበኞችን ፍላጎት ያሟላ እና ጊዜው የሚጠይቀውን የአገልግሎት ዓይነቶች በቀልጣፋ የደንበኞች አገልግሎቱ እያቀረበ መሆኑን አድንቀው፣ ወደፊትም ከዚህ በተሸላ መልኩ አገልግሎት አሰጣጡ እንዲቀጥል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.