ዓባይ ባንክ በጉምሩክ ኮሚሽን ዕውቅና ተሰጠው

ዓባይ ባንክ በጉምሩክ ኮሚሽን ዕውቅና ተሰጠው

ዓባይ ባንክ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የልዩ መብት መታወቂያ የምስክር ወረቀት መጋቢት 26/2015 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል በተከናወነ የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ተቀብሏል፡፡

የልዩ መብት መታወቂያ የምስክር ወረቀቱን የዓባይ ባንክ የዋና ሥራ አስፈጻሚ ከፍተኛ አማካሪ ወ/ሮ እመቤት ስጦታው ከገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ ተቀብለዋል፡፡

በመርሃግብሩ ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ አስመጪዎች፣ ላኪዎች፣ አምራቾች እና የጉምሩክ አስተላላፊዎች በአጠቃላይ 193 ከፍተኛ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች የልዩ መብት መታወቂያ የምስክር ወረቀት የተቀበሉ ሲሆን፣ እውቅና ከተሰጣቸው 10 ባንኮች መካከል ዓባይ ባንክ አንዱ ነው።

የልዩ መብት የተሰጣቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ፕሮግራም ለህግ ተገዥ ለሆኑ ድርጅቶች የተሰጠ መብት እና ደንበኞች ያለምንም እንግልት በሁሉም መንግስታዊ ተቋማት የቅድሚያ እና ፈጣን ልዩ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችልም መሆኑ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.