ዓባይ ባንክ በ12ኛው የኢትዮ – ቻምበር ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒት በመሳተፍ ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ በ12ኛው የኢትዮ – ቻምበር ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒት በመሳተፍ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26/2014 – ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው በ12ኛው የኢትዮ – ቻምበር ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒትና ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

የንግድ ትርዒቱን በይፋ የከፈቱት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ዓባይ ባንክ በኤግዚቢሽን ማዕከል እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ጎብኝተዋል።

የንግድ ትርዒቱ ምርቶችንና አገልገግሎቶችን በማስተዋወቅ ለኢንዱስትሪ ልማት ዕድገት እና ለንግድ ሥራ መስፋፋት አስተዋጽኦ ማበርከትን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ከአዘጋጁ የኢትዮጵያ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡

“የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው የንግድ ትርዒቱ እስከ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለሸማቾችና ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል፡፡

ዝግጅቱ በሀገሪቱ የሚገኙ አምራች፣ አገልግሎት ሰጪ እንዲሁም ዓለምአቀፍ ኩባንያዎች፣ የልማት ድርጅቶች እና ላኪዎች ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለትራንስፖርት፣ ለሆቴልና ቱሪዝም እና ሌሎች ዘርፎች ግብዓት የሚሆኑ ምርት አቅራቢዎች የሚሳተፉበት፣ ሻጭና ሸማች የሚገናኙበት እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚተዋወቁበት መድረክ ነው፡፡

ዓባይ ባንክ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በመላ ሀገሪቱ የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ371 በላይ ያደረሰ ሲሆን፣ በኢንተርኔትና ሞባይል ባንኪንግ ዘርፈ ብዙ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብ ደንበኞቹን እያገለገለ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.