ዓባይ ባንክ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ውጤት በመገመት ሽልማት የሚያስገኝ ውድድር አዘጋጀ

ዓባይ ባንክ በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ውጤት በመገመት ሽልማት የሚያስገኝ ውድድር አዘጋጀ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. በ22ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ጋር በተገናኘ በባንኩ የማህበራዊ ገጾች ላይ ጥያቄዎችን በማቅረብ ትክክለኛውን ውጤት በመገመት የሚያሸልም ውድድር አዘጋጅቷል፡፡

በውድድሩ የሩብ ፍጻሜ፣ ግማሽ ፍጻሜ እና የፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ ቀድመው ውጤቱን በትክክል የገመቱ ተሳታፊዎች ተሸላሚ የሚሆኑ ሲሆን፣ አሸናፊዎቹ ከ2ሺህ ብር እስከ 12 ሺህ ብር መጠን ያለው የዓባይ ባንክ ካርድ ሽልማት ይበረከትላቸዋል፡፡

ተሳታፊዎች ግምታቸውን በዓባይ ባንክ የፌስቡክ ገጽ የመልዕክት መቀበያ (inbox) በመላክ የውድድሩ ተሳታፊ መሆን ይችላሉ፡፡  

በየውድድሩ ምዕራፍ አሸናፊዎቹ ይፋ የሚደረጉ ሲሆን ከፍጻሜው ጨዋታ በኋላ አሸናፊዎቹ ሽልማታቸውን የሚወስዱ ይሆናል፡፡

ዓባይ ባንክ በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ውድድሮች ኅብረተሰቡን የሚያሳትፉ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማዘጋጀት ሽልማቶችን ሲያቀርብ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን፣ በቅርቡ በተካሄደው የ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ተመሳሳይ መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ለአሸናፊዎች ሽልማት ማበርከቱ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.