ዓባይ ባንክ ነባር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላቱን በክብር ሸኘ

ዓባይ ባንክ ነባር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላቱን በክብር ሸኘ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ባንኩን ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ባዘጋጀው ዝግጅት ሽኝት አድርጓል።

ባንኩን በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ ኢትዮጵያ ታደሠ እና ሶስት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

በኘሮግራሙ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላቱ ለባንኩ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ሱፐርቪዥን ዘርፍ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ባስተላለፉት መልዕክት ዓባይ ባንክ እያስመዘገበ የሚገኘውን ሁሉን አቀፍ የሥራ ስኬት አድንቀዋል።

በዕለቱ አዲሱ የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አምላኩ አስረስ ዘውዴ እና አዲስ የቦርድ አባላት ትውውቅ ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.