ዓባይ ባንክ አዲሱን የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ

ዓባይ ባንክ አዲሱን የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ትውውቅ አካሄደ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከ2023/24-2027/28 የሚገለገልበትን የአምስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ በየደረጃው የሚገኙ የባንኩ የሥራ አመራር አባላት በተገኙበት በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደ ዝግጅት ይፋ አደረገ።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እንደተናገሩት ነባራዊውን የዓለምአቀፍ እና የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ ያገናዘበ፣ የባንክ ኢንዱስትሪውን ፈጣን ዕድገት ከግምት ውስጥ ያስገባ፣ የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል፣ ተፎካካሪ እና ውጤታማ የሆነ የስትራቴጂ ዕቅድ መዘጋጀቱን ጠቅሰው፣ ለተግባራዊነቱ ሁሉም የባንኩ ሠራተኞች የድርሻቸውን በመወጣት ስኬታማ ሥራ እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

አቶ የኋላ ገሠሠ ስትራቴጂ ዕቅዱን በማዘጋጀት ለተሳተፉ የስትራቴጂ ዝግጅት ቴክኒክ ቡድን መሪ፣ አስተባባሪ እና የቡድን አባላት ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱም ዕቅዱን በማዘጋጀት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አባላት የዕውቅና ሠርተፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.