ዓባይ ባንክ እና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ እና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመሥራት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ እና አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የውል ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የዓባይ ባንክ የባሕር ዳር ቀጠና ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ሲሳይ ጸጋዬ እና የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ሰጥዬ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች የቤትና የመኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡
ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በመስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ አገልግሎቶችን እያቀረበ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ጨምሮ ለተለያዩ ድርጅቶች ሠራተኞች የብድር አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስምምነት በማድረግ ሰፊ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.