ዓባይ ባንክ እና አዲል ኮርፖሬት ግሩፕ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ እና አዲል ኮርፖሬት ግሩፕ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከአዲል ኮርፖሬት ግሩፕ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አቡበከር ነዚር እና የአዲል ኮርፖሬት ግሩፕ መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አዲል አብደላ ታቢት (ፒኤችዲ) ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ባንኩ በሚሰጠው ሰዲቅ -ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኩል በበርካታ የፋይናንስ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችል እንደሆነ በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ ተጠቅሷል።

አዲል ኮርፖሬት ግሩፕ በውስጡ በግብርና፣ ትምህርት፣ ሆቴልና ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ከአስራ አምስት በላይ ድርጅቶችን በማቀፍ ሀገራዊ ድርሻውን እየተወጣ የሚገኝ ኩባንያ ነው፡፡

ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በማስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ አገልግሎቶችን እያቀረበ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ከላንሴት የሕክምና አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ መድሐኒት ፋብሪካ አ.ማ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ለሌሎችም ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ዘርፈ ብዙ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.