ዓባይ ባንክ ከኢትዮዳሽ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር መስራት ጀመረ

ዓባይ ባንክ ከኢትዮዳሽ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር መስራት ጀመረ

ዓባይ ባንክ ኢትዮዳሽ ከተባለ የገንዘብ አስተላለፊ ድርጅት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ የሐዋላ አገልግሎት መቀበል ጀምሯል፡፡

ዓባይ ባንክ ከኢትዮዳሽ ጋር አብሮ ለመስራት ያደረገው ስምምነት ዜጎችን ኢመደበኛ በሆነው ገንዘብ የማስተላለፍ ሒደት ላይ ሊያጋጥሟቸው ከሚችሉ ሥጋቶች ለመጠበቅና ከውጭ የሚላኩ የውጭ ምንዛሬዎች መደበኛ በሆኑ የባንኩ ሐዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች በመላክ በምንዛሬው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አስተዋፅኦ ማበርከት መቻልን መሰረት ያደረገ ነው፡፡

ኢትዮዳሽ በአሜሪካን አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ ከመላው ዓለም በተለይም ከአሜሪካ የሚላኩ ሐዋላዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የገንዘብ አስተላለፊ ድርጅት ነው፡፡

ዓባይ ባንክ ቀደም ሲል ከዌስተርን ዩኔን፣ ቲዩንስ፣ መኒግራም፣ ድሃብሺል፣ ትራንስ ፋስት፣ ሪያ፣ ዩ-ረሚት፣ ዎርልድ ረሚት፣ ሺፍት፣ ሪሚትሊ እና ኢምራንኤክስቼንጅ ከተባሉ ዓለምአቀፍ የገንዘብ አስተላለፊ ድርጅቶች ጋር በመስራት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.