ዓባይ ባንክ መቻሬ ሜዳ በተዘጋጀው የትንሳዔ ባዛር
ዓባይ ባንክ መቻሬ ሜዳ በተዘጋጀው የትንሳዔ ባዛር

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 04/2014 – ዓባይ ባንክ የ2014 ዓ.ም የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ሳር ቤት አካባቢ በሚገኘው መቻሬ ሜዳ በተዘጋጀው ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም አስታውቋል፡፡

ባንኩ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ድረስ በመቅረብ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋት መሰል ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ ለደንበኞቹ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በመቻሬ ሜዳ የተዘጋጀው ባዛር እስከ ሚያዚያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለሸማቾችና ለጎብኝዎች ክፍት ይሆናል፡፡

ባንኩ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በመላ ሀገሪቱ የቅርንጫፎቹን ብዛት ከ362 በላይ ያደረሰ ሲሆን÷ እንዲሁም በዘመናዊ የባንክ አገልግሎቱ በኢንተርኔትና ሞባይል ባንኪንግ ዘርፈ ብዙ አማራጮችን በማቅረብ ደንበኞቹን እያገለገለ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.