የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች አዲስ የባንኩን ሕንጻ የግንባታ ሒደት ጎበኙ

የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች አዲስ የባንኩን ሕንጻ የግንባታ ሒደት ጎበኙ

የዓባይ ባንክ አ.ማ. ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በግንባታ ላይ የሚገኘውን የባንኩን ግዙፍ ሕንጻ ግንባታ ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ላይ አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ ሌሎች የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

አቶ የኋላ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት የሕንጻው ግንባታ በወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ ግንባታውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ግንባታውን እያከናወነ ካለው ቻይና ው ይ ኃ/የተ ተቋራጭ ድርጅት እና ዠቅአለ የኮማ አማካሪ ድርጅት ጋር የባንኩ የፕሮጄክት ጽሕፈት ቤት ሠራኞች በትጋት እየሠሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የሕንጻው ግንባታ ተጠናቅቆ ሥራ ሲጀምር ለባንኩ ይበልጥ ውጤማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ የኋላ ገልጸዋል፡፡

ሕንጻው ከዋና ዋና አገልግሎቶቹ በተጨማሪ ካፊቴሪያ፣ ጂምናዚየም፣ የሕጻናት ማቆያ፣ የእሳት አደጋ እና የደህንነት መቆጣጠሪያ እንዲሁም የውሃ እና ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎች እንደሚኖሩት በጉብኝቱ ተጠቅሷል፡፡

33 ወለሎች የሚኖሩት ይህ ዘመናዊ ሕንጻ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ግንባታው በአሁኑ ሰዓት 20ኛው ወለል ላይ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.