የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሥልጠና እና ምክክር መድረክ አካሄዱ

የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሥልጠና እና ምክክር መድረክ አካሄዱ

የዓባይ ባንክ አ.ማ. የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ አሥኪያጆች ጋር የሁለት ቀናት የሥልጠና እና የምክክር መድረክ በአምባሳደር ሆቴል አካሂደዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የዓባይ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ አብዱልመናን ከበደ፣ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባል ኡስታዝ ባህሩ ዑመር እና የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባል ሼህ ሰዒድ ኪያር ተገኝተው ከታሳታፊዎች ለተሰነዘሩ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አቶ መሐመድ አሕመድ የዓባይ ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሐብት ማሰባሰብ ሥራ አሥኪያጅ የሸሪዓ ስታንዳርድ እና ኮምፕሊያንስ እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በተመለከተ ለውይይት የሚሆን መነሻ ሐሳብ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ የውይይት መድረኩ እና ሥልጠናው መዘጋጀቱ የሸሪዓ እና ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስቻለ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተመሳሳይ መርሃግብሮች መዘጋጀታቸው አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 7 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በርካታ ደንበኞች በአገልግሎቱ እየተጠቀሙ መሆኑ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.