የዓባይ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ የዋና ግንብ (Main Tower) የመደምደም ሥራ ተጠናቀቀ

የዓባይ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ የዋና ግንብ (Main Tower) የመደምደም ሥራ ተጠናቀቀ

የዓባይ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ የዋናው ግንብ ግንባታ መደምደሚያ ሥራ በትላንትናው ዕለት መጠናቀቁን አብስሯል፡፡

በዕለቱ የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ የህንጻው ግንባታ ተቋራጭ እና አማካሪ ተገኝተው ህንጻው የደረሰበትን ወሳኝ የግንባታ ምዕራፍ ጎብኝተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባንኩ እያስገነባ የሚገኘው ግዙፍ የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመድረሱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ሥራ ሲጀምር ለባንኩ ይበልጥ ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቅሰዋል፡፡

ባንኩ ከዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታው በተጨማሪ በባህር ዳር እና ደሴ ከተሞች እንዲሁም በአዲስ አበባ ለም ሆቴል አካባቢ ተጨማሪ ህንፃዎች እየገነባ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የባንኩን የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ እያከናወነ ያለው የቻይና ዉ ዪ የህንጻ ግንባታ ተቋራጭ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ቺን ጉዝሄን ግንባታውን በታቀደለት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ በትጋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሜክሲኮ አካባቢ በ4ሺህ 591 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውና እየተገነባ ያለው የዓባይ ባንክ ግዙፍ ህንጻ በጠቅላላ 33 ወለሎች አሉት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.