የዓባይ ባንክ የ7ኛ ዙር  የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

የዓባይ ባንክ የ7ኛ ዙር  የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

ዓባይ ባንክ ከነሐሴ 26/2015 ዓ.ም እስከ ጥር 18/2016 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን የቆየው 7ኛው  “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በዚሁም መሠረት ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 46527258 መሆኑ ታውቋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ለሽልማት የተዘጋጁ የ2ኛ ዕጣ እያንዳንዳቸው አስር ፍሪጆች፣ 3ኛ ዕጣ የአስር ቴሌቪዥኖች፣ 4ኛ ዕጣ አስር ላፕቶፖች እና 5ኛ ዕጣ ሃያ ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎች የሚያስገኙ ዕጣዎችም ወጥተዋል፡፡

በዕጣ አወጣጡ ሥነ ሥርዓት ላይ የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮችና  የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለሙያዎችና ታዛቢዎች ተገኝተዋል።

ዓባይ ባንክ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የደንበኞችን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ እንዲሁም ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ በማበረታታት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

የባንኩን የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎችን በቀጣይ የምናሳውቅ ሲሆን፣ ባንኩ ለዕድለኞቸ ከወዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.