የዲያስፖራ ባንኪንግ አገልግሎት

ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ የባንክ አገልግሎት ሲሆን በዋናነት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሠራር ነው፡፡ ይህ አገልግሎት ደንበኞች በውጭ ምንዛሪ በሚከፈት ሒሳብ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት እና በቁጠባ አገልግሎቶቹም ጠቀም ያለ ወለድ የሚያገኙበት ዘዴ ነው፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ባሉበት ሀገር ሆነው ሊገዙ የሚፈልጉትን ቤት ዋጋ  40 በመቶ ሲቆጥቡ ቀሪውን 60 በመቶ ባንኩ ብድር በማመቻቸት ቤቱን እንዲገዙ የሚያስችል ነው፡፡