የዓባይ ባንክ 5ኛ ዙር የ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ – ሥርዓት ተካሄደ

የዓባይ ባንክ 5ኛ ዙር የ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ – ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 07/2014 – ዓባይ ባንክ አ.ማ ከታህሳስ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን የቆየው የባንኩ 5ኛ ዙር የ“ይመንዝሩ፣ ይቀበሉ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በዚሁም መሠረት የ1ኛ ዕጣ የሱዙኪ ዲዛየር ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ቁጥር 2672 መሆኑ ታውቋል፡፡

የሽልማት ዓይነቶች

1ኛ ዕጣ ሱዙኪ ዲዛየር ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል

2ኛ ዕጣ አምስት ከ 200-350 ሊትር የሚይዙ ሳምሰንግ ፍሪጆች

3ኛ ዕጣ አምስት ሳምሰንግ 32 ኢንች ቴሌቪዥኖች

4ኛ ዕጣ አምስት ኤችፒ ላፕቶፖች

5ኛ ዕጣ አስር ሁዋዌ የሞባይል ቀፎዎች ለዕጣ አሸናፊ ዕድለኞች ወጥተዋል፡፡

በቀጣይ ባሉት ጥቂት ቀናት የባንኩን 5 ዙር የ“ይመንዝሩ፣ ይቀበሉ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም ዕድለኞችን የምናሳውቅ ሲሆን፣ ባንኩ ከወዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.