ተዘዋዋሪ/ ታዳሽ የብድር አቅርቦት

ባንኩ አገልግሎቱን በማስፋት አሁን ያለውን ወይም የወደፊቱን የገበያ ፍላጎቶች እና የደንበኞቹን ጥያቄዎች ባገናዘበ መልኩ ዘርፈ ብዙ የብድር አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ የአገልግሎቶቹ ዓይነት እና ተፈጥሮ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡-

ሀ. ‘ኦቨርድራፍት’ የብድር አቅርቦት

ይህ የብድር አገልግሎት አዋጪነት እና ቀጣይነት ባለው የንግድ ሥራ ለተሰማሩ ደንበኞች ለዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው በባንኩ ካላቸው የተቀማጭ ሒሳብ ገንዘብ በላይ እንዲወስዱ የሚፈቀድበት አሠራር ነው፡፡ደንበኞች ከባንኩ የወሰዱትን ቀሪ ገንዘብ ባንኩ በጠየቀ ጊዜ የሚመልሱ ሲሆን ፣ በመደበኛነት ከአንድ ዓመት ላልበለጠ ጊዜ የሚሰጥ ሆኖ ለአዳዲስ ደንበኞች እና ብድሩን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማያውሉ ደንበኞች ለስድስት ወራት ያህል ብቻ የሚፈቀድ ይሆናል፡፡

ለ. ጊዜያዊ‘ኦቨርድራፍት’

ይህ አገልግሎት ደንበኞች የሚገጥማቸውን ወቅታዊ እና ያልተጠበቀ የገንዘብ እጥረት ለማሟላት እንዲሆን በባንኩ ካላቸው ተቀማጭ ሒሳብ በላይ የገንዘብ መጠን ለመሳብ የሚያስችል ለአጭር ጊዜ የሚፈቀድ የብድር አገልግሎት ነው፡፡

ሐ.  ‘ኦቨርድራዋል’ አገልግሎት

‘ኦቨርድራዋል’ አገልግሎት ደንበኞች ለሚገጥማቸው ወቅታዊ እና ያልተጠበቀ የገንዘብ እጥረት ከሚፈቀድላቸው የ‘ኦቨርድራፍት’ መጠን በላይ የተወሰነ ገንዘብ እንዲወስዱ መብት የሚሰጥ ጊዜያዊ የብድር አቅርቦት ሲሆን፣ ይህም ከሚፈቀደው የ‘ኦቨርድራፍት’ መጠን ገደብ ከ25% መብለጥ የለበትም፡፡

መ. የሸቀጣ ሸቀጥ ብድር አቅርቦት

የሸቀጣ ሸቀጥ ብድር በባንኩ የሚሰጥ የአጭር-ጊዜ የብድር አገልግሎት ሲሆን ሸቀጣ ሸቀጥ (ለሽያጭ ዓላማ የተመረተ ወይም የተገዛን ምርት ወይም የተለያዩ ዕቃዎችን) ወይም የሰነድ ማስረጃ (የባቡር፣ የመጋዘን ወይም የአየር መንገድ ደረሰኞችን) ለብድሩ እንደ ዋስትና በመያዝ የሚሰጥ ነው፡፡Ø  የዚህ አገልግሎት ዓላማ ደንበኞች ገንዘባቸው በሸቀጣ ሸቀጥ ሲያዝባቸው ከሚገጥማቸው የጥሬ ገንዘብ እጥረትእንዲላቀቁ ማድረግ ነው፡፡

ባንኩ የአንድ ጊዜ ወይም በየጊዜው የሚታደስ የሸቀጣ ሸቀጥ ብድር አቅርቦት ሊሰጥ ይችላል፡፡

ሰ. የገቢ ንግድ ሰነድ ብድር አቅርቦት

የገቢ ንግድ ሰነድ ዓባይ ባንክ በአስመጪነት የንግድ ሥራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አመልካቾች ወይም ለተለያየ ዓላማ ዕቃ ለሚያስመጡ አካላት የብድር ሰነድ ሲከፍቱ የሰነዱን ዋጋ የተወሰነውን መቶኛ በመክፈል የሚያቀርበው የብድር አገልግሎት ነው፡፡Ø  በደንበኛው የፋይናንስ ጥንካሬ የብድር ሰነድ ሒሳብ አፈፃፀም እና ከውጭ በሚገቡት ዕቃዎች የገበያ ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ባንኩ የገቢ ንግድ ሰነዶቹን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ ለደንበኛው ቢያንስ የገቢ ንግድ ሰነዱን ዋጋ 30% ያህል የብድር አቅርቦት ለአንድ ዓመት የሚሰጠው ይሆናል፡፡Ø  ባንኩ የአንድ ጊዜ እና/ ወይም በየጊዜው የሚታደስ የገቢ ንግድ ሰነድ ብድር አቅርቦት ሊሰጥ ይችላል፡፡

ረ. የቅድመ-ጭነት የወጪ-ንግድ የብድር አቅርቦት

ይህ አገልግሎት ግብዓቶችን እና ጥሬ ዕቃዎችን ለመግዛት ፣ ለማቀነባበርና ወደ የተጠናቀቁ ዕቃዎች ለመቀየር ፣ መጋዘን ውስጥ ለማስቀመጥ እንዲሁም ሸቀጦቹን ለማሸግ እና እስከሚጫኑበት ጊዜ ድረስ ለማጓጓዝ የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው፡፡  ባንኩ የብድር አገልግሎቱን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተገኘ ዋስትና ፣ የተረጋገጠ የሽያጭ ውል፣ የወጪ ንግድ ሰነድ ወይም የቅድመ – ክፍያ ሰነድ ላይ ተመርኩዞ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

ሠ.  በየጊዜው የሚታደስ የወጪ ንግድብድርአቅርቦት

ይህ አገልግሎት ላኪዎች ከጭነት ማረጋገጫ ሰነድ በስተቀር ተቀባይነት ያላቸውን ትክክለኛ የወጪ ንግድ ሰነዶች ሲያቀርቡ የሚሰጥ የብድር አቅርቦት ነው፡፡  በየጊዜው የሚታደስ የወጪ ንግድ ብድር አቅርቦት የሚፈቀድላቸው በወጪ ንግድ ታሪካቸው  ንፁህ ሪከርድ ላላቸው ላኪዎች ብቻ ነው፡፡  የወጪ-ንግድ ‘ቢል’ቅድመ-ክፍያ  የወጪ-ንግድ ‘ቢል’ ቅድመ-ክፍያ- ለድኅረ-ጭነት የወጪ-ንግድ የሚሰጥ ብድር ሲሆን ፣ ላኪዎች ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ የወጪ-ንግድ ሰነዶች አሟልተው ሲያቀርቡ በሸቀጦቹ ጭነት ወቅት ያለውን የመሥሪያ ካፒታል ፍላጎት ለማሟላት ነው፡፡  የወጪ-ንግድ ‘ቢል’ ቅድመ-ክፍያ አገልግሎት ለአሥራ አምስት (15) ቀናት ሊፈቀድ ይችላል።