ዓባይ ባንክ እና ላንሴት የሕክምና አገልግሎት የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ እና ላንሴት የሕክምና አገልግሎት የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከላንሴት የሕክምና አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር ጋር መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የዓባይ ባንክ የሪቴይል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ አሰፋ ተፈራ እና የላንሴት የሕክምና አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሄኖክ ሰይፈ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የላንሴት የሕክምና አገልግሎት ኃ/የተ/የግል ማህበር ሠራተኞች የቤት እና መኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡

ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በማስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ አገልግሎቶችን እያቀረበ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ሕብረት፣ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ፣ ዳሽን ቢራ አ.ማ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና ለሌሎችም ድርጅቶች የብድር አገልግሎት በመስጠት ሠራተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.