ዓባይ ባንክ ለ6ኛ ዙር ያዘጋጀው የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ

ዓባይ ባንክ ለ6ኛ ዙር ያዘጋጀው የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ

ዓባይ ባንክ አ.ማ የ6ኛ ዙር “የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት  የካቲት 17/2015 ዓ.ም በኃይሌ ግራድ አዲስ አበባ ሆቴል አከናውኗል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኃላ ገሠሠ የፕሮግራሙ  ዋና አላማ የደንበኞችን የቁጠባ ባህል ለማጎልበትና በባንኩ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት በመጠቀም ህጋዊ የገንዘብ ምንዛሬን ለማበረታታት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ባንኩ በአሁኑ ሰዓት ከ2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ዋና ስራ አስፈፃሚው ጨምረው  ተናግረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው የዕጣው አሸናፊዎች የባንኩ አምባሳደሮች መሆናቸውን በመጥቀስ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የ6ኛ ዙር  “የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የ1ኛ ዕጣ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል መኪና አሸናፊ የሆኑት በመምህርነት የሙያ ዘርፈ ላይ በማገልገል  የሚገኙት የአጅባር ከተማ ነዋሪ አቶ ቶፊቅ አሰፋ ሲሆኑ÷ ዕድለኛ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ዓባይ ባንክ ቃሉን ጠብቆ ሽልማቱን ስላስረከባቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በሽልማት መርሀ ግብሩ ላይ ባንኩ ለባለዕድለኞች ያዘጋጀው የዕጣ ዓይነቶች 1ኛ ዕጣ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል፣ 2ኛ ዕጣ 10 የማቀዝቀዣ ማሽኖች ወይም ፍሪጆች፣ 3ኛ ዕጣ 10 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ 4ኛ ዕጣ 10 ቴሌቪዥኖች እና 5ኛ ዕጣ 20 ስማርት የስልክ ቀፎዎች ናቸው፡፡ ዓባይ ባንክ ለ6ኛ ጊዜ  ያዘጋጀው “የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ የሸለሙ” ፕሮግራም ከነሐሴ 26/2014 ዓ.ም እስከ ጥር 19/2015 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.