ዓባይ ባንክ 272ኛ ቅርንጫፉን በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ዓባይ ባንክ 272ኛ ቅርንጫፉን በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ዓባይ ባንክ 272 ቅርንጫፉን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጊና አገር ከተማ መንሀሪያ አጠገብ “ጊና አገር ቅርንጫፍ” በሚል ስያሜ መጋቢት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

ቅርንጫፉ የባንኩ ሥራ አስፈፃሚዎች እና የየአካባቢዎቹ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቀው ተከፍተዋል ፡፡

ቅርንጫፉ ተመርቆ ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከባንኩ የኮር ባንኪንግ ሥርዓት ጋር በኔትወርክ የተሳሰሩ ሲሆን፣ ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከተለመደው በተለየ መልኩ ረዘም ላሉ የሥራ ሰዓታት ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዓባይ ባንክ ደንበኞቹን ያሉበት ድረስ ቀርቦ ለማገልገል በማለም በቅርቡ ቅርንጫፎቹን በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች እንደሚያስፋፋ ሲገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ዓባይ – ታማኝ አገልጋይ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.