ዓባይ ባንክ 276ኛ ቅርንጫፉን በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ዓባይ ባንክ 276ኛ ቅርንጫፉን በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ዓባይ ባንክ 276 ቅርንጫፉን በአማራ ክልል ደራ ወረዳ ሀሙሲት ከተማ  መንሀሪያዉ መግቢያ አካባቢ “ሐሙሲት ቅርንጫፍ” በሚል ስያሜ ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

ቅርንጫፉ የባንኩ ሥራ አስፈፃሚዎች እና የየአካባቢዎቹ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቀው ተከፍተዋል ፡፡

ቅርንጫፉ ተመርቆ ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከባንኩ የኮር ባንኪንግ ሥርዓት ጋር በኔትወርክ የተሳሰሩ ሲሆን፣ ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከተለመደው በተለየ መልኩ ረዘም ላሉ የሥራ ሰዓታት ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዓባይ ባንክ ደንበኞቹን ያሉበት ድረስ ቀርቦ ለማገልገል በማለም በቅርቡ ቅርንጫፎቹን በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች እንደሚያስፋፋ ሲገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ዓባይ – ታማኝ አገልጋይ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.