የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት

የዓባይ ባንክ የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኞች ገንዘባቸውን በማንኛውም ስፍራ እና ጊዜ በመረጃ መረብ (ኢንተርኔት) በመጠቀም ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችላቸው አገልግሎት ነው፡፡ በዓባይ ባንክ የኢንተርኔት ባንኪንግ የሚያገኟቸው አገልግሎቶች፡-

  • ቀሪ ሒሳብዎን ማወቅ፣
  • የባንክ ሒሳብዎን ዝርዝር መግለጫ ማግኘት፣
  • ገንዘብ ማስተላለፍ፣
  • የብድር ጥያቄ ማቅረብ፣
  • ብድርዎ ያለበትን ሁኔታ መረጃ ማግኘት፣
  • የኤ.ቲ.ኤም. ካርድዎን መረጃ ማወቅ፣
  • የኤ.ቲ.ኤም. ካርድዎን ማንቀሳቀስ እና ማስቆም፣
  • የአዲስ ካርድ ጥያቄ እና ምትክ ካርድ መጠየቅ፣
  • የቼክ ደብተር መጠየቅና ማስቆም፣
  • ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈፀም፣
  • የዕለቱንና ያለፉትን ቀናት የውጭ ገንዘቦች ምንዛሪ መረጃ ማግኘት፣
  • የደመወዝ ክፍያ መፈፀም::

 

ወደ ኦንላይን ባንኪንግ ይሂዱ