የዓባይ ባንክ የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

የዓባይ ባንክ የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

ዓባይ ባንክ ከነሐሴ 26/2014 ዓ.ም እስከ ጥር 19/2015 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን የቆየው “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በዕጣ አወጣጡ ሥነ ሥርዓት ላይ አቶ ወንድይፍራው ታደሰ የዓባይ ባንክ የስትራቴጂ እና ማርኬቲንግ ዋና መኮንን እንደተናገሩት የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የደንበኞችን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ እንዲሁም ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሆነውን የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲጠቀሙ ማበረታታትን ዓላማ ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በዚሁም መሠረት ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 12222151 መሆኑ ታውቋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ለሽልማት የተዘጋጁ የ2ኛ ዕጣ እያንዳንዳቸው አስር ፍሪጆች፣ 3ኛ ዕጣ የአስር ቴሌቪዥኖች፣ 4ኛ ዕጣ አስር ላፕቶፖች እና 5ኛ ዕጣ ሃያ ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎች የሚያስገኙ ዕጣዎችም ወጥተዋል፡፡ የባንኩን የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎችን በቀጣይ ጥቂት ቀናት የምናሳውቅ ሲሆን፣ ባንኩ ለዕድለኞቸ ከወዲሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.