የጊዜ ገደብ ብድር

የጊዜ ገደብ ብድር ለመሥሪያ ካፒታል እና/ ወይም ፕሮጀክት ፋይናንስ ለማድረግ በተወሰነ ወለድ ምጣኔ ለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ ብድር ሲሆን ፣ አከፋፈሉም በንግዱ ሁኔታ እና በገንዘብ ፍሰት ላይ በመመርኮዝ የብድሩ ጊዜ ሲደርስ ሙሉውን በአንድ ጊዜ መክፈል ወይም በየወቅቱ (ማለትም በየወሩ ፣ በየሩብ ዓመቱ ፣ በየስድስት ወር ወይም በየአመቱ) ሊሆን ይችላል።

ሀ. የአጭር ጊዜ ብድር

የአጭር ጊዜ ብድር ባንኩ የተበዳሪውን የመሥሪያ ካፒታል ፍላጎት ወይም ሌሎች ጊዜያዊ የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ እጥረቶችን ለመቅረፍ ለአንድ ዓመት ወይም ከዚያ ላነሰ ጊዜ የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው፡፡

ለ. የመካከለኛ ጊዜ ብድር

የመካከለኛ ጊዜ ብድር ከአንድ ዓመት ረዘምላለ እና ከአምስት ዓመት ለማይበልጥ ጊዜ የሚሰጥ ብድር ሲሆን፣ አከፋፈሉም በቋሚነት ወቅታዊ ክፍያዎችን የሚያካትት ነው፡፡ የመካከለኛ ጊዜ ብድር የሥራ ካፒታል ፍላጎትን ለማሟላት ወይም ቋሚ ንብረቶችን ለመግዛት ሊውል ይችላል፡፡

ሐ. የመካከለኛ ጊዜ ብድር

በሌላ በኩል የረጅም ጊዜ ብድር ከአምስት ዓመት በላይ ለሚረዝም እና ከ20 ዓመታት ለማይበልጥ ጊዜ ለንግድ ዓላማ የሚውል ብድር ሲሆን ፣ ይህም በየጊዜው የሚከፈል ይሆናል፡፡የረጅም ጊዜ ብድር በዋናነት የፕሮጀክት ፋይናንሲንግ ባህሪ አለው፡፡

መ. የሞተር ተሽከርካሪ ግዥ ብድር

የሞተር ተሽከርካሪ ብድር በትራንስፖርት ወይም በሌሎች የንግድ ዘርፎች ያለውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ለሞተር ተሽከርካሪዎች መግዣ የሚውል በጊዜ ገደብ የሚሰጥ ብድር ሲሆን ፣ የሚገዛው ተሽከርካሪ በዋስትናነት የሚያዝ እና በሚመለከተው የመንግስት አካል የተመዘገበ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

ሠ. የግንባታ ማሽኖች ግዥ ብድር

የግንባታ ማሽኖች ብድር ለግንባታ የሚያስፈልጉ ማሽኖችን፣ ማለትም የጭነት መኪና ፣ ዶዘር ፣ ግሬደር ፣ ሎደር ፣ ኤክስካቫተር ፣ ስክራፐር ፣ ሮለር ፣ አስፋልት ፔቨር ፣ ክረሸር ፣ የኮንክሪትባች መሥሪያ ፣ የኮንክሪት ፔቨር ፣ ክሬን ፣ የቁፋሮ መሣሪያዎች ፣ ዋገን ድሪል እና ቺፕስ ፕሪደሮችን ለመግዛት በጊዜ ገደብ የሚሰጥ ብድር ነው፡፡

የሚገዙት የግንባታ ማሽኖች በዋስትናነት የሚያዙ ሆነው፣ በሚመለከተውየመንግስትአካልየተመዘገቡ መሆንአለባቸው፡፡

ረ. የህንፃ ግንባታ ብድሮች.

የህንፃ ግንባታ ብድር የንግድ ሕንፃ ለመገንባት ፣ ለማደስ ወይም ለመግዛት ዓላማ የሚሰጥ የብድር ዓይነት ሲሆን ፣ ብድሩ የግንባታውን ወይም የግዢውን ወጪ በከፊል ሊሸፍን ይችላል፡፡

የብድሩ ዓላማ ለኪራይ ፣ ለሽያጭ ፣ ለሌላ የንግድ ሥራ ፣ ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሌላ አዋጭ የንግድ ሥራ ሊሆን ይችላል፡፡

ሰ. የግንባታሥራ ካፒታል ብድር (ድልድይ ብድሮች)

የግንባታ ሥራ ካፒታል ብድር ተቋራጮች ከአሠሪዎች ጋር በሚፈፅሙት ውል ላይ ተመሥርቶ የመሥሪያ ካፒታል እጥረትን ለመቅረፍ ፈቃድ ላላቸው ተቋራጮች የሚሰጥ ብድር ሲሆን፣ ይህም ለውስብስብ ሕንፃዎች ፣ መንገዶች ፣ ግድቦች ፣ ለመሳሰሉት ማስፈፀሚያ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ይውላል፡፡

የብድር አቅርቦቱ በንብረት ማስያዣ ወይም ያለ ማስያዣ ሊሰጥ ይችላል፡፡