Category: <span>ዜና</span>

ዓባይ ባንክ ከኢትዮዳሽ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር መስራት ጀመረ
Post

ዓባይ ባንክ ከኢትዮዳሽ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅት ጋር መስራት ጀመረ

ዓባይ ባንክ ኢትዮዳሽ ከተባለ የገንዘብ አስተላለፊ ድርጅት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ የሐዋላ አገልግሎት መቀበል ጀምሯል፡፡ ዓባይ ባንክ ከኢትዮዳሽ ጋር አብሮ ለመስራት ያደረገው ስምምነት ዜጎችን ኢመደበኛ በሆነው ገንዘብ የማስተላለፍ ሒደት ላይ ሊያጋጥሟቸው ከሚችሉ ሥጋቶች ለመጠበቅና ከውጭ የሚላኩ የውጭ ምንዛሬዎች መደበኛ በሆኑ የባንኩ ሐዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች በመላክ በምንዛሬው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አስተዋፅኦ ማበርከት መቻልን...

ዓባይ ባንክ በ2015 የአዲስ ዓመት ባዛር በመሳተፍ ላይ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ በ2015 የአዲስ ዓመት ባዛር በመሳተፍ ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው የ2015 አዲስ ዓመት ዋዜማ ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ባንካችን ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ሲሆን፣ በኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ጳጉሜን 05/2014 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

ዓባይ ባንክ እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ሕብረት የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ
Post

ዓባይ ባንክ እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ሕብረት የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ሕብረት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ሕብረት አባላት እና ሠራተኞች በባንኩ በመቆጠብ የቤት እና መኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር እንዲያገኙ የሚያስችል ይሆናል፡፡ ስምምነቱን የዓባይ ባንክ ተጠባባቂ ዋና – ሪቴል ባንኪንግ መኮንን አቶ ማርቆስ...

ዓባይ ባንክ እና ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ
Post

ዓባይ ባንክ እና ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ የጋራ ሥራ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21/2014 – ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሠ አሰፋ ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ. ሠራተኞች...

ዓባይ ባንክ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ሰጠ
Post

ዓባይ ባንክ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች እውቅና ሰጠ

ዓባይ ባንክ ለሁለት ቀናት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ባካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ በ2021/22 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ቅርንጫፎች እና ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች ከባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና የዳይሬክተሮች የቦርድ አባላት ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡ የባህርዳር ቀጠና ጽሕፈት ቤት ባስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም የአንደኛ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን፣ የአዝዋ፣ አምደወርቅ፣ አራትኪሎ፣ ቋራ እና ስታዲየም ቅርንጫፎች የእውቅና ሰርተፊኬት እና የማበረታቻ የገንዘብ...

ዓባይ ባንክ ለ5ኛው ዙር “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ
Post

ዓባይ ባንክ ለ5ኛው ዙር “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች ሽልማት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28/2014 – ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለ5ኛው ዙር የ“ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም አሸናፊዎች የሽልማት አሰጣጥ ሥነሥርዓት ዛሬ አከናውኗል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እንደገለጹት በባንኩ የውጭ ምንዛሬ አገልግሎት መጠቀም መቻል ሕገወጥ የገንዘብ ምንዛሬን ለመከላከል ያግዛል፤ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ መጎልበት የጎላ አስተዋጽኦ ያበረክታል፤ እንዲሁም ደንበኞች ባንኩ የሚሰጣቸውን በርካታ አገልግሎቶች እንዲላመዱ...

ዓባይ ባንክና ዳሽን ቢራ አ.ማ. ሠራተኞች ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
Post

ዓባይ ባንክና ዳሽን ቢራ አ.ማ. ሠራተኞች ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16/2014- ዓባይ ባንክ ለዳሽን ቢራ አ.ማ. ሠራተኞች የቤት እና መኪና መግዣ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር ከባንኩ እንዲያገኙ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የዳሽን ቢራ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ማሪዮ ቫን ገርደር በተገኙበት በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል በዛሬው ዕለት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በማስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ...

የዓባይ ባንክ 5ኛ ዙር የ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ – ሥርዓት ተካሄደ
Post

የዓባይ ባንክ 5ኛ ዙር የ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ – ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 07/2014 – ዓባይ ባንክ አ.ማ ከታህሳስ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን የቆየው የባንኩ 5ኛ ዙር የ“ይመንዝሩ፣ ይቀበሉ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በዚሁም መሠረት የ1ኛ ዕጣ የሱዙኪ ዲዛየር ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ቁጥር 2672 መሆኑ ታውቋል፡፡ የሽልማት ዓይነቶች 1ኛ ዕጣ ሱዙኪ ዲዛየር...

ዓባይ ባንክ በ12ኛው የኢትዮ – ቻምበር ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒት በመሳተፍ ላይ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ በ12ኛው የኢትዮ – ቻምበር ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒት በመሳተፍ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26/2014 – ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው በ12ኛው የኢትዮ – ቻምበር ዓለምአቀፍ የንግድ ትርዒትና ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ የንግድ ትርዒቱን በይፋ የከፈቱት የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ዓባይ ባንክ በኤግዚቢሽን ማዕከል እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ጎብኝተዋል። የንግድ ትርዒቱ ምርቶችንና አገልገግሎቶችን በማስተዋወቅ ለኢንዱስትሪ ልማት ዕድገት እና ለንግድ...