Author: Abay (Administrator )

የዓባይ ባንክ የ7ኛ ዙር  የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ
Post

የዓባይ ባንክ የ7ኛ ዙር  የ“ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

ዓባይ ባንክ ከነሐሴ 26/2015 ዓ.ም እስከ ጥር 18/2016 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን የቆየው 7ኛው  “ይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በዚሁም መሠረት ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 46527258 መሆኑ ታውቋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ለሽልማት የተዘጋጁ የ2ኛ ዕጣ እያንዳንዳቸው አስር ፍሪጆች፣ 3ኛ ዕጣ የአስር ቴሌቪዥኖች፣ 4ኛ ዕጣ...

ለውድ ደንበኞቻችን በሙሉ፣
Post

ለውድ ደንበኞቻችን በሙሉ፣

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ዘመኑ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ግብዓት በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን እና የተቀላጠፈ የደንበኞች አገልግሎትን ለመስጠት ቅዳሜ የካቲት 9/2016 ዓ.ም. የሲስተም ማሻሻያ ሥራ ያከናውናል፡፡በመሆኑም ከላይ በተጠቀሰው ቀን አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን ለውድ ደንበኞቻችን በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን፡፡ ዓባይ – ታማኝ አገልጋይ!

የዓባይ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ የዋና ግንብ (Main Tower) የመደምደም ሥራ ተጠናቀቀ
Post

የዓባይ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ የዋና ግንብ (Main Tower) የመደምደም ሥራ ተጠናቀቀ

የዓባይ ባንክ የዋና መሥሪያ ቤት ህንጻ የዋናው ግንብ ግንባታ መደምደሚያ ሥራ በትላንትናው ዕለት መጠናቀቁን አብስሯል፡፡ በዕለቱ የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ የህንጻው ግንባታ ተቋራጭ እና አማካሪ ተገኝተው ህንጻው የደረሰበትን ወሳኝ የግንባታ ምዕራፍ ጎብኝተዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባንኩ እያስገነባ የሚገኘው ግዙፍ የዋና መሥሪያ ቤት...

ዓባይ ባንክ የ2016 የግማሽ ዓመት የሥራ አመራር አባላት ስብሰባ አካሄደ
Post

ዓባይ ባንክ የ2016 የግማሽ ዓመት የሥራ አመራር አባላት ስብሰባ አካሄደ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. የ2016 ዓ.ም. የግማሽ ዓመት የሥራ አመራር አባላት ስብሰባ በኃይሌ ግራንድ ሆቴል አካሂዷል፡፡ በስብሰባው ላይ አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ የባንኩ አጠቃላይ  የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በጥልቀት መካሄዱ ታውቋል፡፡

ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ የገና ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ የገና ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው የ2016 የገና ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡ በባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ታኅሣሥ 27/2016 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

ዓባይ ባንክ በገና ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል
Post

ዓባይ ባንክ በገና ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው የ2016 የገና ባዛር ላይ በመሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ጎብኝዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡ በኤግዚቢሽን ማዕከል እና ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ የተከፈተው ባዛር እስከ ታኅሣሥ 27/2016 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች አዲስ የባንኩን ሕንጻ የግንባታ ሒደት ጎበኙ
Post

የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች አዲስ የባንኩን ሕንጻ የግንባታ ሒደት ጎበኙ

የዓባይ ባንክ አ.ማ. ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በግንባታ ላይ የሚገኘውን የባንኩን ግዙፍ ሕንጻ ግንባታ ጎበኙ፡፡ በጉብኝቱ ላይ አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ ሌሎች የባንኩ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ አቶ የኋላ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት የሕንጻው ግንባታ በወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ ግንባታውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ግንባታውን እያከናወነ ካለው ቻይና ው ይ ኃ/የተ ተቋራጭ ድርጅት...

ዓባይ ባንክ ለፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
Post

ዓባይ ባንክ ለፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ለሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ብር 360,000.00 ድጋፍ አደረገ፡፡ ድጋፉን አቶ አቡበከር ነዚር የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠባባቂ ምክትል ዋና መኮንን ለዶ/ር አሚን መሐመድ አሊ የሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ በክፍለ ከተማው በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ አስረክበዋል፡፡ ድጋፉ የክፍለ...

ዓባይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
Post

ዓባይ ባንክ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. በዋግ ኸምራ እና በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን እርዳታ የሚውል የአስር ሚሊየን ብር ድጋፍ በዛሬው ዕለት አደረገ። ድጋፉን አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ የአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት (አመልድ) ዋና ዳይሬክተር አስረክበዋል፡፡ ዓባይ ባንክ በተለያዩ ጊዜያት በሀገራችን ተከስተው ለነበሩ ማኅበራዊ ቀውሶች ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን ሲያሳይ...

ዓባይ ባንክ እና የፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
Post

ዓባይ ባንክ እና የፉሪ ክ/ከተማ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን አቶ አቡበከር ነዚር የዓባይ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት  ተጠባባቂ ምክትል ዋና መኮንን እና ዶ/ር አሚን መሐመድ አሊ የሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ተፈራርመዋል፡፡ ...