ሌሎች የቁጠባ አገልግሎቶች

ጥበብ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት

ደንበኞች ለራሳቸው ወይም ለልጆቻቸው የትምህርት ወጪን ለመሸፈን የሚያስችላቸው እና ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኝ ለትምህርት ወጪ መሸፈኛ የሚውል የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ነው፡፡

ክለብ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶች

ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኙ እና የበዓል ማክበሪያ እና የመዝናኛ ወይም የጉዞ ቁጠባ ሒሳብ በመባል በሁለት የሚከፈሉ ናቸው፡፡

  • የበዓል ቁጠባ ሒሳብ፡- ደንበኞች ለግል ፍጆታቸው ወይም ለቤተሰብ፣ ለበዓላት ወይም ለተለያዩ ዝግጅቶች ላልታሰቡ ወጪዎች እንዳይዳረጉ እና ቀድሞ በማቀድ በዓላቱን ወይም ዝግጅቶቹን ከቤተሰብ፣ ከወዳጅ እና ከዘመድ ጋር በደስታ እንዲያሳልፉ የሚያስችል የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን፣ ቁጠባው በተናጠል ወይም በቡድን ሊደረግ የሚችል ነው፡፡ ባንኩ ለዚህ የቁጠባ ሒሳብ በቆይታው ጊዜ መጠን የሚታሰብ ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስብ ሲሆን፣ ይህም ደንበኞች ያሰቡትን ዝግጅት ወይም በዓል በተሳካ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ይረዳል፡፡
  • የመዝናኛ ወይም የጉዞ ቁጠባ ሒሳብ፡- ደንበኞች በተናጠል ወይም በቡድን ለሚያደርጓቸው ጉብኝቶች ወይም ለመዝናናት ሲያስቡ ቀድመው በማቀድ እና በመቆጠብ ጠቀም ያለ ወለድ የሚያገኙበት የቁጠባ አገልግሎት ዓይነት ነው፡፡

ከላይ በቀረቡት በሁለቱም የቁጠባ ሒሳብ አማራጮች ከውጭ ሀገር በሚላክ የውጭ ምንዛሪ ለሚቆጥቡ ደንበኞች ባንኩ ተጨማሪ  የተሻለ ወለድ ያስባል፡፡

ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት

ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት በባንኩ በተዘጋጀ ሳጥን ገንዘብ ጥቂት – በጥቂት በማጠራቀም በተወሰነ ወቅት ወደ ባንኩ በማምጣት ለማስቀመጥ የሚያስችል የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሰናይ የቁጠባ አገልግሎት

ይህ የቁጠባ ሒሳብ በሃገሪቱ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶአቸው በበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማሩ ተቋማትን ማዕከል ያደረገ እና ተቋማቱ በባንካችን በሚከፍቱት ሒሳብ አማካኝነት የበጎ አድራጎት ስራዉን በመደግፍ እና ከመደበኛው የቁጠባ አገልግሎቶች በተለየ መልኩ የተለየ የወለድ ምጣኔ ማዕቀፍ በማዘጋጀት፤ እንዲሁም ለጋሽ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በባንኩ ካላቸው የተቀማጭ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ስራዉ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችላቸውን አሰራር ያመቻቸ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡

ጥሪት የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት

ጥሪት የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ዕድሜያቸው 50 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ወደፊት ለሚኖሯቸው ዘመናት ዋስትና እንዲሆናቸው የሚቆጥቡበት እና ጠቀም ያለ የወለድ የሚያስገኝ አገልግሎት ነው፡፡

ተስፋ የቁጠባ ሒሳብ

ባንካችን በተለያዩ ምክንያቶች ከአገራቸው ተሰደው በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ዜጎች ከመደበኛው የቁጠባ አገልግሎት በተለየ ሁኔታ “ተስፋ” በሚል ስያሜ አዲስ የቁጠባ አገልግሎትን በማቅረብ ደንበኞችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

ሙሉ መረጃውን በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ በመቅረብ ይውሰዱ።

ጎጆ የቁጠባ ሒሳብ

ባንካችን ለእጮኛሞች እና ለባለትዳሮች ጎጇቸውን ለማሞቅና የተለያዩ ጉዳዮቻቸውን ማከናወኛ እንዲቆጥቡ በማለም ከመደበኛው የቁጠባ አገልግሎት ጠቀም ያለ ወለድ የሚከፈልበት “ጎጆ” በሚል ስያሜ አዲስ የቁጠባ አገልግሎት በማቅረብ ደንበኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል።

ሙሉ መረጃውን በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ በመቅረብ ይውሰዱ።

ሱመያ – ከወለድ ነጻ የሴቶች የቁጠባ ሒሳብ

ባንካችን የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችንና አሰራሮችን መሰረት በማድረግ “ሱመያ – ከወለድ ነጻ የሴቶች የቁጠባ ሒሳብ” በሚል ስያሜ አዲስ የቁጠባ አገልግሎት በማቅረብ ደንበኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል።

ሙሉ መረጃውን በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ወዲዓ – ከወለድ ነጻ የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ

ባንካችን የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ በማለም የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችንና አሠራሮችን መሰረት ያደረገ “ወዲዓ – ከወለድ ነጻ የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ” በሚል ስያሜ አዲስ የቁጠባ አገልግሎት በማቅረብ ደንበኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል።

ሙሉ መረጃውን በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ዕድር – የቁጠባ ሒሳብ

በሀገራችን ረጅም ዘመናትን ካስቆጠሩና ማኅበራዊ መስተጋብርን በእጅጉ ካጎለበቱ የማኅበረሰብ እሴቶቻችን ውስጥ ዕድር ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

ባንካችን የዚህን ቀደምት ማኅበራዊ እሴት ጉልህ ፋይዳ በመገንዘብ እና ማህበራዊ ጥቅሙን ከግምት በማስገባት ለዕድር ማኅበራት ከመደበኛው የቁጠባ ሒሳብ ተጨማሪ ወለድ እና ሌሎች ጥቅሞችን የሚያስገኝ “ዕድር – የቁጠባ ሒሳብ” በማቅረብ ደንበኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል።

ሙሉ መረጃውን በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ዕቁብ – የቁጠባ ሒሳብ

በሀገራችን ረጅም ዘመናትን ካስቆጠሩና ማኅበራዊ መስተጋብርን ካጎለበቱ የማኅበረሰብ እሴቶቻችን ውስጥ ዕቁብ በዋናነት ይጠቀሳል።

ባንካችን የዚህን ቀደምት ማኅበራዊ እሴት ጉልህ ፋይዳ በመገንዘብ ከመደበኛው የቁጠባ ሒሳብ ተጨማሪ ወለድ እና ሌሎች ጥቅሞችን የሚያስገኝ “ዕቁብ – የቁጠባ ሒሳብ” በማቅረብ ደንበኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በደስታ ይገልጻል።

ሙሉ መረጃውን በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡