ሌሎች የቁጠባ አገልግሎቶች

ጥበብ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት

ደንበኞች ለራሳቸው ወይም ለልጆቻቸው የትምህርት ወጪን ለመሸፈን የሚያስችላቸው እና ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኝ ለትምህርት ወጪ መሸፈኛ የሚውል የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ነው፡፡

ዓባይ የስጦታ ካርድ ሒሳብ አገልግሎት

ደንበኞች ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ እና ለዘመድ ስጦታ መስጠት ሲፈልጉ የዓባይ ስጦታ ካርድን በመጠቀም ከብር 00 ጀምሮ በመስጠት፣ ተቀባዩ ሲፈልግ በጥሬ ገንዘብ ካልሆነም ካርዱን በመጠቀም ከባንኩ ጋር በጥምረት ከሚሠሩ መደብሮች የሚፈልጉትን ዕቃ መሸመት የሚችሉበት የአገልግሎት ዓይነት ነው፡፡

ክለብ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎቶች

ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኙ እና የበዓል ማክበሪያ እና የመዝናኛ ወይም የጉዞ ቁጠባ ሒሳብ በመባል በሁለት የሚከፈሉ ናቸው፡፡

  • የበዓል ቁጠባ ሒሳብ፡- ደንበኞች ለግል ፍጆታቸው ወይም ለቤተሰብ፣ ለበዓላት ወይም ለተለያዩ ዝግጅቶች ላልታሰቡ ወጪዎች እንዳይዳረጉ እና ቀድሞ በማቀድ በዓላቱን ወይም ዝግጅቶቹን ከቤተሰብ፣ ከወዳጅ እና ከዘመድ ጋር በደስታ እንዲያሳልፉ የሚያስችል የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን፣ ቁጠባው በተናጠል ወይም በቡድን ሊደረግ የሚችል ነው፡፡ ባንኩ ለዚህ የቁጠባ ሒሳብ በቆይታው ጊዜ መጠን የሚታሰብ ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስብ ሲሆን፣ ይህም ደንበኞች ያሰቡትን ዝግጅት ወይም በዓል በተሳካ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ይረዳል፡፡
  • የመዝናኛ ወይም የጉዞ ቁጠባ ሒሳብ፡- ደንበኞች በተናጠል ወይም በቡድን ለሚያደርጓቸው ጉብኝቶች ወይም ለመዝናናት ሲያስቡ ቀድመው በማቀድ እና በመቆጠብ ጠቀም ያለ ወለድ የሚያገኙበት የቁጠባ አገልግሎት ዓይነት ነው፡፡

ከላይ በቀረቡት በሁለቱም የቁጠባ ሒሳብ አማራጮች ከውጭ ሀገር በሚላክ የውጭ ምንዛሪ ለሚቆጥቡ ደንበኞች ባንኩ ተጨማሪ  የተሻለ ወለድ ያስባል፡፡

ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት

ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት በባንኩ በተዘጋጀ ሳጥን ገንዘብ ጥቂት – በጥቂት በማጠራቀም በተወሰነ ወቅት ወደ ባንኩ በማምጣት ለማስቀመጥ የሚያስችል የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሰናይ የቁጠባ አገልግሎት

ይህ የቁጠባ ሒሳብ በሃገሪቱ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቶአቸው በበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማሩ ተቋማትን ማዕከል ያደረገ እና ተቋማቱ በባንካችን በሚከፍቱት ሒሳብ አማካኝነት የበጎ አድራጎት ስራዉን በመደግፍ እና ከመደበኛው የቁጠባ አገልግሎቶች በተለየ መልኩ የተለየ የወለድ ምጣኔ ማዕቀፍ በማዘጋጀት፤ እንዲሁም ለጋሽ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በባንኩ ካላቸው የተቀማጭ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ስራዉ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችላቸውን አሰራር ያመቻቸ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡

ጥሪት የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት

ጥሪት የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ዕድሜያቸው 50 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ግለሰቦች ወደፊት ለሚኖሯቸው ዘመናት ዋስትና እንዲሆናቸው የሚቆጥቡበት እና ጠቀም ያለ የወለድ የሚያስገኝ አገልግሎት ነው፡፡