የደንበኛ ሒሳቦች

ተቀማጭ የቁጠባ ሒሳብ

ተቀማጭ የቁጠባ ሒሳብ ወለድ የሚያስገኝ የአገልግሎት ዓይነት ሲሆን፣ ይህንን ሒሳብ ለመክፈት ዝቅተኛው ተቀማጭ ገንዘብ ብር 25.00/ ሃያ አምስት ብር/ ሆኖ፣ ነገር ግን ሂሳቡን በዜሮም መክፈት የሚቻል ሲሆን፣ በዚህ አግባብ የሚከፈት ሂሳብ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሂሳቡ ላይ ብር 25.00/ ሃያ አምስት ብር/ እና ከዚያ በላይ ገቢ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ማንኛውም ደንበኛበአንዱ ቅርንጫፍ የከፈተውን ሒሳብ በየትኛውም የዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ ማንቀሳቀስ ይችላል፡፡

ተንቀሳቃሽ ሒሳብ

ይህ አገልግሎት ወለድ የማይታሰብበት በቼክ የሚንቀሳቀስ የሒሳብ ዓይነት ነው፡፡ ይህን ሒሳብ ለመክፈት ለግለሰቦች ወይም በግል ለሚተዳደሩ ነጋዴዎች ብር 250.00/ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር መነሻ ተቀማጭ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ ለማኅበራት እና መሰል ድርጅቶች ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር ያስፈልጋል፡፡

የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ሒሳብ

ይህ የሒሳብ ዓይነት ከደንበኛው ጋር በሚደረግ ስምምነት ለተወሰነ የጊዜ ገደብ የሚቀመጥ ሲሆን ዋናውና ወለዱ እስከ ጊዜ ገደቡ መጨረሻ ድረስ የሚቆይ ከሆነ በስምምነቱ መሠረት ገንዘቡ ጠቀም ያለ ወለድ ያስገኛል፡፡ ለዚህ ሒሳብ ዝቅተኛ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 100,000.00/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ ነው፡፡

ወለድ የሚያስገኝ ልዩ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ

ይህ ሒሳብ ወለድ የሚያስገኝ ተንቀሳቃሽ የሒሳብ ዓይነት ነው፡፡ ሒሳቡን ለመክፈት የሚያስፈልገው ዝቅተኛው ተቀማጭ ገንዘብ ብር 1,000.00/ አንድ ሺህ ብር/ ሲሆን፣ ሒሳቡን ለማንቀሳቀስ የባንክ ሒሳብ ደብተር አያስፈልግም፡፡ በምትኩ ለደንበኛው የቼክ ደብተር ይዘጋጅለታል፡፡ ከብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በታች ለሆነ ተቀማጭ ገንዘብ ወለድ የማይታሰብ ሲሆን፣ ወለድ ለማግኘት በወር ከሦስት ጊዜ በላይ ገንዘብ ወጪ ማድረግ አይፈቀድም፡፡

ፕሮቪደንት ፈንድ ሒሳብ

የድርጅቶችን ፕሮቪደንት ፈንድ በተቀማጭነት አስቀማጩ የሚያዝበት የቁጠባ ሒሳብ ዓይነት ነው፡፡

የውጭ ምንዛሪ ሒሳብ

የውጭ ምንዛሪ ሒሳብ አገልግሎት የገንዘብ ምንጩ ከሀገር ውጭ ሆኖ ሒሳቡ የሚከፈተው በሀገር ውስጥ ብር ምንዛሪ ይሆናል፡፡

የሒሳቡም ዓይነት፡-

  • የሀገር ውስጥ ያልሆነ የማይዘዋወር፣
  • የሀገር ውስጥ ያልሆነ የሚዘዋወር፣
  • የሀገር ውስጥ ያልሆነ የሚዘዋወር የውጭ ምንዛሪ፣
  • የዲያስፖራ ሒሳብ ናቸው፡፡

የሀገር ውስጥ ሐዋላ አገልግሎት

ዓባይ ባንክ በሁለም ቅርንጫፎቹ ለደንበኞቹ ፈጣን እና ቀልጣፋ የሀገር ውስጥ ሐዋላ አገልግሎት ይሰጣል፡፡