የካፒታል ገበያን አስመልክቶ ለዓባይ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ እና ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ሥልጠና ተሰጠ

የካፒታል ገበያን አስመልክቶ ለዓባይ ባንክ የዳሬክተሮች ቦርድ እና ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ሥልጠና ተሰጠ

ለዓባይ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት የካፒታል ገበያን በተመለከተ በዛሬው ዕለት በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በመጡ ከፍተኛ የካፒታል ገበያ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ላይ ዶ/ር አምላኩ አስረስ የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እንዲሁም አቶ የኋላ ገሠሠ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተገኝተዋል፡፡

አቶ የኋላ በስልጠናው ላይ እንደተናገሩት የካፒታል ገበያን ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ሽግግር ባንኩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅቶች በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን÷ስልጠናው መዘጋጀቱ አስፈላጊነቱ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ስልጠናውን ዓባይ ባንክ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጋር በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.