ዓባይ ባንክ ከፍተኛ አመታዊ ገቢ አስመዘገበ

ዓባይ ባንክ ከፍተኛ አመታዊ ገቢ አስመዘገበ

ዓባይ ባንክ በ2015 በጀት ዓመት 7.1 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ አስመዘገበ። ይህ የተገለፀው የባንኩ የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል ዛሬ በተካሄደበት ወቅት ነዉ።

በጉባዔው ላይ የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አምላኩ አስረስ የባንኩ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ የ29 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት በማስመዝገብ ብር 41.8 ቢሊዮን መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ባንኩ የደንበኞቹን ቁጥር የ49 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት በማሳየት በዓመቱ መጨረሻ ላይ 2.5 ሚሊዮን ያደረሰ ሲሆን የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት በበጀት ዓመቱ 110 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ከፍቷል፡፡

የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ በበኩላቸው   በ2015 በጀት ዓመት ባንኩ ከግብር በፊት ብር 2.1 ቢሊዮን በማትረፍ ባንኩን ወደ አዲስ ከፍታ መውሰድ መቻሉን አብስረዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ካከናወናቸው ዓበይት ጉዳዮች መካከል “ጉዞ ከፍታ” የተሰኘው የአምስት ዓመት የመሪ ዕቅድ ዝግጅት እንደሚገኝበት ጠቅሰው፣ አዲሱ መሪ እቅድ ከ2016 እስከ 2021ዓ.ም. ድረስ እንደሚቆይ ገልፀዋል ፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በበጀት ዓመቱ ለተመዘገበው ውጤት የበኩላቸውን ላበረከቱ ባለድርሻ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.