ሌሎች ብድሮች

ሀ. ከፊል የገንዘብ ድጋፍ

ባንኩለሽያጭ ወይም ለሐራጅ ያቀረባቸውን ንብረቶች ለመግዛት ለሚፈልጉ የንብረቶቹን ዋጋ በከፊል የሚሸፍንበት የፋይናንስ አሠራር ነው፡፡Ø  እነዚህ ንብረቶችም በዋስትና የተያዙ ወይም በባንኩ የተረሱ ህንፃዎች ፣ተሽከርካሪዎች ፣ ማሽኖች እና የንግድ ተቋማት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ለ. ሲንዲኬት ብድር

ሲንዲኬት ብድር ከገንዘቡ መጠን ከፍተኛነት እና ተያይዞ ሊያስከትል ከሚችለው ስጋት አንፃር ባንኩ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመጣመር በጋራ የሚሰጠው የጊዜ ገደብ ብድር ዓይነት ሲሆን ፣ በአብዛኛው ብድሩ የሚሰጠው ከመካከለኛ እስከ ረዥም ለሚደርስ ጊዜ ነው፡፡Ø  የሲንዲኬት (ተባባሪ) ብድር ዓላማ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመሆን ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁ የመካከለኛ ወይም የረጅም ጊዜ የኢንቬስትመንት አማራጮችን በደቦ ፋይናንስ በማድረግ ፣ ስጋትን ማከፋፈል እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት ችግርን መቀነስ ነው፡፡ የገንዘብ አቅርቦቱ ቋሚ ንብረቶችን ለመግዛት እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ለሚያስፈልገው የመሥሪያ ካፒታል ሊውል ይችላል፡፡

ሐ.  የከተማ መገልገያዎች ፋይናንሲንግ

ይህ አገልግሎት በከተሞች የደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ አያያዝ ፣ የእንሰሳት እርድ ፣ የህዝብ አምቡላንስ ፣ የእሳት አደጋ መከላከል ፣ የጎዳና ላይ መብራት ፣ የመንገድ አስፋልት እና ንጣፍ ሥራዎች ፣ የንፅህና አጠባበቅ ፣ የሕዝብ መፀዳጃ ቤት፣የስነ-ውበት ሥራዎች ፣ የህዝብ መዝናኛ ማዕከላት ልማት (ፓርኮች ፣ ሲኒማ ቤቶች ፣ የጥበብ ጋለሪዎች ፣ ቴያትር ቤቶች ፣የስፖርት ማእከሎች) ፣ ታሪካዊ ቦታዎችን እና መታሰቢያዎችን ማልማት እና ጠብቆ ማቆየት (ሐውልቶች፣ታሪካዊ ግንቦች፣ ቤተ-መንግስቶች፣ የተለያዩ ቅርሶች፣ወዘተ) የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት የመሳሰሉልዩ-ልዩ አገልግሎቶችን ለሚያቀርቡ ማዘጋጃ ቤቶች እናግ ለሰቦች በጊዜ ገደብ የሚሰጥ የብድር ዓይነትነው፡፡

መ.  የአማካሪ ድርጅት ፋይናንሲንግ

ይህ አገልግሎት እንደ ምህንድስና ፣ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፣ሕግ ፣የሒሳብ ሥራ ፣አስተዳደር ፣አርኪቴክቸር ፣ስነ-ጥበብ ፣ወዘተ ያሉ ሙያዊ አገልግሎቶች ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የንግድ ሥራን ለማስኬድ በጊዜ ገደብ የቀረበ የመሥሪያ ካፒታል ብድር ዓይነት ነው፡፡

ሰ. የንግድ ሀሳብ / የፈጠራ ሥራ ፋይናንሲንግ

የንግድ ሀሳብ/ የፈጠራ ሥራ ፋይናንሲንግ በሚመለከተውየመንግስት አካል ወይም ስመጥር ዓለምአቀፋዊ ድርጅት ለተረጋገጡ እና ዕውቅና ለተሰጣቸው የፈጠራ ሀሳብ/ ሥራ ባለቤት የሆኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ሳይንሳዊ ጥናቶችን  እንዲያካሂዱ እና ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችሉለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ የብድር አገልግሎት ነው፡፡Ø  ብድሩ ከአእምሮአዊ ንብረት መብት ጥበቃ ጽ/ቤት እና/ወይም ከታወቀ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ዕውቅና ያገኘውን የፈጠራ ሀሳብ በጅም ላለማምረት እና ገበያ ላይ ለማዋል ሊሰጥ ይችላል፡፡

ረ.  የመሣሪያ / የማሽነሪሊዝ ፋይናንሲንግ

የመሣሪያሊዝ ፋይናንሲንግ በንግድ ሥራ እንቅስቃሴያቸው ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎችን መከራየት/ በሊዝማግኘት ለሚፈልጉ ደንበኞች የሚሰጥ በጊዜ የተገደበ የብድር ዓይነት ነው፡፡ ተንቀሳቃሽመሣሪያዎቹ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ንብረቶችን (የመሬትማ ስተካከያ ማሽኖችን፣የግንባታ ተሽከርካሪዎችን ፣የምርት መሰብሰቢያዎችን እና ትራክተሮችን ወዘተ) ያካትታሉ፡፡

ሠ. የገቢ ንግድሰነድ የብድርማስያዣደብዳቤ

ይህ አገልግሎት ደንበኞች በመሥሪያ ካፒታል እጥረት ምክንያት እጃቸው ላይ የሚገኝን የገቢ ንግድ ሰነድ (import letter of credit)ማጣራት ሲያቅታቸው፣ በሰነዱ ዋጋ ተመን ላይ ተመሥርቶ ለተበዳሪዎች የገቢ ንግድ ሰነዱን ወደ የጊዜ ገደብ ብድር (Term Loan) ወይም የሸቀጣሸቀጥ ብድር (Merchandise Loan) በመቀየር የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው፡፡· ባንኩ ከውጭ በመጡት ዕቃዎች ዓይነት እና በደንበኛው የብድር ስጋት ደረጃ ላይ በመመስረት ብድሩን በዋስትና ወይም ያለዋስትና ሊሰጥ ይችላል፡፡

ሸ. የብድር ግዢ

የብድር ግዢ ባንኩ ከሌሎች ባንኮች ብድር የሚገዛበት የአሠራር ዓይነት ሲሆን ፣ባንኩ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፈው የብድር ግዢውንትርፋማነት ካመነበት ብቻነው፡፡

ቀ. የገቢዎች ቅናሽ/ የክፍያ መጠየቂያ ፋይናንስ

ይህ አገልግሎት ንግድ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች የሚሰጥ ሆኖ፣ ከሌሎች ድርጅቶች ወይም የንግድ ሰዎች  የሚቀበሉት ክፍያ ወይም የሚጠበቁት ገንዘብ ላይ ተመሥርቶ የሚሰጥ የብድር ዓይነት ነው፡፡በጊዜያዊ የገንዘብ እጥረት ምክንያት በብድር የተሸጡ ሸቀጦች ከገዢው ክፍያ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ደንበኞች በተረጋገጡ የክፍያ የምስክር ወረቀቶች ከሌሎች ድርጅቶች ወይም ከንግድ ሰዎች የሚጠበቁ ደረሰኞች ወይም ክፍያዎች ላለው የንግድ ሰውለተወሰነ ጊዜ የሚሰጥ የብድርዓይነት ነው፡፡

በ. ከላይ ከተጠቀሱት የብድር አገልግሎቶች በተጨማሪ ፣ ባንኩ እነዚህን የብድር አገልግሎቶች በተጨማሪነት ይሰጣል፡

  • የመጋዘን ደረሰኝ ፋይናንሲንግ
  • በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ዲያስፖራዎች የቤት ብድር
  • ለተራድኦ ተቋማት ደንበኞች ብድር
  • ለተቀዳሚ ድርጅት ሰራተኞች የሚውል የኮንሲውመር ብድር
  • የውጭ ሰራተኞች እና የቢዝነስ ተቋም ባለቤቶች የሚውል የኮንሲውመር ብድር ነው፡፡