እንቡጥ ቁጠባ አገልግሎት

እንቡጥ የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ዓይነት ወላጆች/አሳዳጊዎች/ ለልጆቻቸው ለሚያሳድጉት ልጅ የሚከፈት የቁጠባ ሒሳብ ዓይነት ነው፡፡ አገልግሎቱ ወላጆች ለልጆቻቸው የቁጠባ ባሕል እንዲያዳብሩ ለማስተማር የሚረዳ ሲሆን፣ ከፍ ባለ ወለድ ገንዘብ እንዲቆጥቡ ያስችላል፡፡

  • ሒሳቡ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ የሚከፈት ነው፤
  • ሒሳቡ በወላጆች ወይም በአሳዳጊዎች የሚከፈት እና የሚንቀሳቀስ ነው፤
  • የህፃናት ቁጠባ ሒሳብ 7.5% ወለድ ያስገኛል፡፡