የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት

የዓባይ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ደንበኛው ሒሳቡን በሞባይል ስልክዎ በኩል ማንቀሳቀስ እንዲችል ያደርጋል፡፡ ይህ የሞባይል ስልክ አገልግሎት ሒሳብዎን በማንኛውም ጊዜ እንዲሁም ቦታ ማንቀሳቀስ ያስችላል። የዓባይ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ የሚሰጥዎ አገልግሎት፡-

 • ገንዘብ መላክ፣
 • ያለዎትን ቀሪ ሒሳብ ማወቅ፣
 • አጭር የሒሳብ መግለጫ፣
 • ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈፀም፣
 • የቼክ ጥያቄ እና የቼክ ክፍያን ማገድ፣
 • ካርድዎን ማገድ እና መፍቀድ፣
 • የሞባይል አየር ሰዓት መሙላት፣
 • ዕለታዊ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማወቅ፣
 • ገንዘብ ወደ ራስዎ ወይም ወደ ሌላ ሰው ማስተላለፍ፣
 • ገንዘብ ወጪ ማድረግ፣
 • የብድርዎን ሁኔታ ማወቅ፣
 • የአውሮፕላን ቲኬት ክፍያ መፈፀም፡፡

 

የዓባይ ባንክ ሞባይል መተግበሪያ ለአንድሮይድ ያውርዱ

የዩኤኤስዲ አጠቃቀም መመሪያ ያውርዱ