ንግሥት ቁጠባ አገልግሎት
ይህ አገልግሎት የሴቶችን ፍላጎት ያማከለ ሲሆን፣ ሴቶችን የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች
አሉት፡፡
የሴቶች ልዩ የቁጠባ ሒሳብ ከሌሎች የሚለየው፡-
- ሒሳቡ በሴቶች ብቻ እንዲከፈት የተፈቀደ ነው፤
- ሒሳቡ በግለሰብ፣ በጣምራ ወይም በማኅበር ደረጃ መከፈት ይችላል፤
- ሒሳቡ በቅድሚያ በባዶ ሊከፈት ይችላል፤ ነገር ግን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብር 25.00/ ሃያ አምስት ብር ገንዘብ ሊኖረው ይገባል፤
- የሒሳቡ ባለቤቶች 7.215% ወለድ ያገኛሉ፤
- የሒሳቡ ባለቤቶች በማንኛውም ጊዜ የፈለጉትን ገንዘብ መጠን ማውጣት ይችላሉ፡፡