የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት
የዓባይ ባንክ የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኞች ገንዘባቸውን በማንኛውም ስፍራ እና ጊዜ በመረጃ መረብ (ኢንተርኔት) በመጠቀም ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ የሚያስችላቸው አገልግሎት ነው፡፡ በዓባይ ባንክ የኢንተርኔት ባንኪንግ የሚያገኟቸው አገልግሎቶች፡-
- ቀሪ ሒሳብዎን ማወቅ፣
- የባንክ ሒሳብዎን ዝርዝር መግለጫ ማግኘት፣
- ገንዘብ ማስተላለፍ፣
- የብድር ጥያቄ ማቅረብ፣
- ብድርዎ ያለበትን ሁኔታ መረጃ ማግኘት፣
- የኤ.ቲ.ኤም. ካርድዎን መረጃ ማወቅ፣
- የኤ.ቲ.ኤም. ካርድዎን ማንቀሳቀስ እና ማስቆም፣
- የአዲስ ካርድ ጥያቄ እና ምትክ ካርድ መጠየቅ፣
- የቼክ ደብተር መጠየቅና ማስቆም፣
- ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያዎችን መፈፀም፣
- የዕለቱንና ያለፉትን ቀናት የውጭ ገንዘቦች ምንዛሪ መረጃ ማግኘት፣
- የደመወዝ ክፍያ መፈፀም::