የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት

የባንኩን ኤ.ቲ.ኤም. (የመክፍያ ማሽን) በመጠቀም ደንበኞች በማንኛውም ስፍራ እና ጊዜ እንዲሁም በማንኛውም ባንክ የገንዘብ መክፈያ ማሽን ገንዘባቸውን በካርድ ማንቀሳቀስና ግብይት መፈፀም የሚያስችላቸው አገልግሎት ነው፡፡

የዓባይ ካርድን በመጠቀም የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያገኛሉ፡፡

  • ገንዘብ ወጪ ማድረግ፣
  • ቀሪ ሒሳብዎን ማወቅ፣
  • አጭር የሒሳብ መግለጫ ማግኘት፣
  • የባንክ ሒሳብዎን ዝርዝር መግለጫ ማግኝት፣
  • ገንዘብ ማስተላለፍ፣
  • የቼክ ደብተር መጠየቅ፣
  • የተከፋይ ቼክን ክፍያን ማገድ፣
  • ያለ ካርድ ገንዘብ መላክና መቀበል፣
  • እንዲሁም ሌሎችም በርካታ አገልግሎቶች ይገኙበታል፡፡