የወጣቶች ቁጠባ አገልግሎት

ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ እንደመሆናቸው መጠን እንደ ቤተሰብ አስተዳዳሪ፣ እንደ ሠራተኛ እንዲሁም እንደ ማኅበረሰብ አገልጋይነታቸው የሚያሳልፉት ውሳኔ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም ዓባይ ባንክ ለወጣቶች ልዩ የቁጠባ ሒሳብ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡

ይህ ሒሳብ ከሌሎች የሚለየው፡-

  • ሒሳቡ ዕድሜያቸው ከ18 – 24 በሆኑ ወጣቶች የሚከፈት ነው፡፡
  • ሒሳቡ በተመሳሳይ የዕድሜ ክልል በሚገኙ ወጣቶች በግል ወይም በቡድን ሊከፈት ይችላል፡፡
  • የወጣቶች ቁጠባ ሒሳብ 7.215% ወለድ ያስገኛል፡፡
  • ሒሳቡ በቅድሚያ በባዶ ሊከፈት ይችላል፤ ነገር ግን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብር 25.00/ ሃያ አምስት ብር/ እና ከዚያ በላይገንዘብ ሊኖረው ይገባል፡፡
  • የሒሳቡ ባለቤቶች በማንኛውም ጊዜ የፈለጉትን ገንዘብ መጠን ማውጣት ይችላሉ፡፡