የዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ

የዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ ባንኩ ለደንበኞቹ በጽሁፍ የሚሰጠው የማይሻር ዋስትና ሲሆን፣አመልካቹየባንኩ ደንበኛ በውል ስምምነቱ ላይ በሰፈረው መልክ ደንብ እና ግዴታውን አክብሮየማይወጣ ከሆነ፣ባንኩ ለተጠቃሚው ወገን (የሀገርውስጥምሆነየውጭ) የገንዘብ ካሳለመክፈል ቃል የሚገባበት አሠራር ነው፡፡ ባንኩለደንበኞች የአንድ ጊዜ ወይም በየጊዜው የሚታደስ የዋስትና ደብዳቤ ሊሰጥ ይችላል፡፡Ø  ባንኩ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ደንበኞች የዋስትና አገልግሎትይሰጣል፡፡

ሀ. የጨረታ ማስከበሪያ/ ማስያዣ ዋስትና

በተጫራች ጥያቄ መሠረት ባንኩ ለተጠቀሰው ተጠቃሚ/ጨረታ ለሚያወጣው አካል ደህንነት የሚሰጠው ዋስትና ሲሆን፣ ከባንኩ ዋስትናውን የገዛው ተጫራች ከውድድሩ በሚወጣበት ጊዜ ከተጠቃሚው /ጨረታውን ካወጣው አካል ሊቀርቡ የሚችሉትን አቤቱታዎችለማሟላትየሚሰጥ የዋስትና አገልግሎት ነው፡፡ዋስትናውንከባንኩየገዛው ተጫራጭ በጨረታውወቅትአሸናፊ ሆኖ በሚገኝበት ወቅት ጨረታዉን ላለመቀበል በሚወስንበት ጊዜ ለጨረታ አውጪው የሚከፈል የዋስትና አይነት ነው፡፡

ለ. የአፈፃፀም ቦንድ ዋስትና

በጨረታ ያሸነፈ አካል በውል ስምምነቱ ላይ በሰፈረው መልኩ የተወዳደረበትን ዕቃ ካላስረከበ ወይም አገልግሎቱን ካላቀረበ፣ በጨረታው አደራጅ(ተጠቃሚ) የሚቀርበውን ማንኛውንም ጥያቄ እንደሚያሟላ በባንኩ የሚሰጥ ዋስትናነው፡፡

ሐ. የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና

ይህ የዋስታና አይነት ቅድመክፍያውን ለከፈለው ገዢ የሚሠጥ የዋስትና አይነት ሲሆን ቅድመክፍያውን የሚያገኘው ሻጭ/ተቃራጭ የቅድሚያክፍያውንካገኘ በኃላ በተለያየ ምክንያት አገልግሎት ለመስጠት ለተስማማበት እቃ/አገልግሎት በውሉ መሰረት ማቅረብ ሳይችል ሲቀር ባንኩ በስምምነቱ መሰረት ክፍያውን ለመመለስ የሚደረግ የዋስትና አይነት ነው፡፡

መ. የአቅራቢዎች የብድር ዋስትና

በሀገርውስጥደንበኛ (ባለዕዳ) ስምሌላ የሀገርውስጥወይምየውጭአቅራቢ (ተጠቃሚ) ደህንነትን ለማስጠበቅ ባንኩ የሚሰጠው ዋስትና ሲሆን፣ይህም የሀገር ውስጥ ገዢው (ተበዳሪው) በውሉላይ የሰፈሩትን ደንብ እና ግዴታዎች መፈፀም ካልቻለ ባንኩ በተጠቃሚው በኩል የሚቀርበውን ማናቸውንም የይገባኛል ጥያቄ ለማሟላት ቃል የሚገባበት አሠራር ነው፡፡

ሰ. የማቆያ/የይዞታ ዋስትና

የማቆያ/የይዞታ ዋስትና ሻጭ ወይም ተቋራጭየገባውን ግዴታ ሳይወጣ ሲቀር ሻጩ ወይም ተቋራጩ በጠየቀ ጊዜ በውል ስምምነቱ ላይ በሰፈረው መልኩ ደንብ እና ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ ይዞታውን ለተጠቃሚው ለመልቀቅ የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡

ረ. የጉምሩ ክግዴታ ዋስትና

ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የገቡ ዕቃዎች እንደገና ወደ ውጭ እንደማይላኩ እና ለጉምሩ ክባለሥልጣን ተገቢው ቀረጥ ያልተከፈለባቸው መሆኑን ገልፆ ባንኩ የተጠቃሚውን (ጉምሩክ ባለሥልጣን) መብት ለማረጋገጥ ለተጠቃሚው የሚሰጠው የዋስትና ዓይነትነው፡፡