የውክልና ባንኪንግ አገልግሎት

የዓባይ ውክልና ባንክ አገልግሎት በዋናነት የባንክ አገልግሎት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አገልግሎት ነው። የውክልና ባንክ አገልግሎቱ “ዓባይ በደጄ” በሚል ስያሜ ደንበኞቹ ባሉበት አካባቢ በቅርበት ያገለግላል፡፡ የዓባይ በደጄ አገልግሎት ባንኩ እውቅና በሚሰጣቸው ወኪሎች አማካይነት የሚሰጥ ሲሆን እነዚህም፡- ሱቆች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ ፋርማሲዎች እና ሌሎች የመገበያያ አማራጮች ናቸው፡፡

በእነዚህ ውክልና በተሰጣቸው አካላት በኩል የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፡-

  • መደበኛ የቁጠባ ሒሳብ፣
  • የሞባይል ሒሳብ መክፈት፣
  • በተከፈተው ሞባይል ሒሳብ ገቢና ወጪ ማድረግ፣
  • ለልዩ-ልዩ አገልግሎቶች እና ግዢዎች ክፍያ መፈፀም፣
  • ገንዘብ መላክ እና መቀበል፣
  • የሞባይል አየር ሰዓት መሙላት፣… ናቸው፡፡