የገቢ ንግድ አገልግሎቶች

ባንኩ ከውጭ ሀገራት ለሚገቡ ሸቀጦችን የውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ለመስጠት  በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር FXD / 07/98 መሰረት የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች ያስተናግዳል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ፈቃዱ ከተገኘ በኋላ የማስመጣት ግብይቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ፣ በባንኩ ፖሊሲዎች እና አሠራሮች እና በዓለም አቀፍ ሕግጋቶች ይከናወናሉ፡፡

በዚህም መሠረት ዓባይ ባንክ የሚከተሉት የክፍያ ዓይነቶች ለገቢ ንግድ ፈቃድ ይሰጣል፡፡

  • የገቢ ንግድ መተማመኛ ሰነድ
  • የገቢ ንግድ ክፍያ ሰነድ
  • የገቢ ንግድ ቅድሚያ ክፍያ
  • ፍራንኮ ቫሉታ