ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የትንሣዔ ባዛር ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የትንሣዔ ባዛር ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል

ዓባይ ባንክ የ2015 ዓ.ም የትንሣዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ባዛር ላይ በመሳተፍ ለጎብኝዎችና ለተሳታፊዎች በባዛሩ ላይ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የባዛሩ ታዳሚ ደንበኞች የሚያስፈልጋቸውን የባንክ አገልግሎቱን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡ መጥተው እንዲጎበኙን ጋብዘንዎታል፡፡ 

ዓባይ ባንክ ለደንበኞች አመቺ በሆኑ ጊዜ እና ቦታዎች ላይ በመገኘት ዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎትን በመስጠት ላይ ሲሆን÷ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀው የትንሣዔ ባዛር ላይ በመሳተፍም ተመሳሳይ የባንክ አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡   

በሚሊኒየም አዳራሽ “ዩቶፒያ ኢስተር ኤክስፖ-2023” በሚል በሐበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን እና በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል “ሰላም ፋሲካ-ኤክስፖ 2023” በሚል በሴንቸሪ ፕሮሞሽን የተዘጋጁት የትንሣዔ ባዛሮች እስከ ሚያዚያ 07/2015 ዓ.ም ለጎብኝዎች ክፍት ሆነው ይቆያሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.