ስለ ዓባይ ሰዲቅ

የዓባይ ሰዲቅ (ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት) የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆዎችን እና አሠራሮችን በመከተል በአገልግሎት ወቅት ምንም ዓይነት ወለድ መክፈልም ሆነ መቀበል ላይ ያልተመሠረተ እንዲሁም በሸሪዓው ህግ በተፈቀዱ የሥራ ዘርፎች ላይ ብቻ የሚሳተፍ እና የራሱ የሆነ አሠራር የሚከተል የባንክ አገልግሎት ነው፡፡

ዓባይ ባንክ አ.ማ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱን ዓባይ ሰዲቅ ብሎ በመሰየም አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግም ለዚሁ ተግባር ብቻ በተዘጋጁ እና ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን የሚሰጡ ቅርንጫፎችን በመክፍት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በሁሉም ቅርንጫፎች ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎት ብቻ በሚሰጡ መስኮቶች ደንበኞች አገልግሎቱን ማግኘት እንደችሉ በማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡