ተቋማዊ ፍልስፍና

ራዕያችን

      ቀዳሚ ተመራጭ ባንክ መሆን!

 

ተልዕኳችን

     የላቀ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የባለድርሻ አካላትን ዕሴት ማሳደግ

 

እሴቶቻችን

     ደንበኛ ተኮርነት

     ተጠያቂነት

     በቡድን መስራት

     ሠራተኛ ተኮርነት

     ፈጠራ

 

መርሃችን

     ዓባይ -ታማኝ አገልጋይ!

 

የባንኩ አመራርና አስተዳደር

ዓባይ ባንክ የሚመራው በጠቅላላ ጉባዔ በተመረጡ የቦርድ አባላት ሲሆን፣ ተጠሪነታቸውም በቀጥታ ለጠቅላላ ጉባዔው ነው፡፡ የቦርዱ አመራር ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የባንክ አገልግሎት እንዲፈጠር በማድረግ የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ለማሳደግ ተግቶ ይሠራል፡፡ የዓባይ ባንክ የበላይ አመራር አባላትም በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ እና በትምህርት ዝግጅታቸውም ብቁና ተወዳዳሪ ናቸው፡፡ ዓባይ ባንክ እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 30/2023 ድረስ ከ8,626/ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስድስት/ በላይ ሠራተኞች ቀጥሮ በማሠራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከሁሉም በበለጠ የባንኩ አመራር እና ሠራተኞች የባንኩን ራዕይና ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ በቁርጠኝነትና በትጋት ይሠራሉ፡፡