ዓባይ ባንክ 269ኛ እና 270ኛ ቅርንጫፎቹን ከፈተ
ዓባይ ባንክ 269ኛ እና 270ኛ ቅርንጫፎቹን ከፈተ

ዓባይ ባንክ 269 ቅርንጫፉን በምስራቅ ጎጃም ዞን በሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ ጤና ጣቢያዉ አጠገብ “የጁቤ ቅርንጫፉ”  በሚል ስያሜ የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

ተያይዞም በተመሳሳይ ቀን 270 ቅርንጫፉን በአዲስ አበባ ከተማ መካኒሳ ኮንዶሚኒየም አካባቢ “መካኒሳ ቅርንጫፍ”  በሚል ስያሜ የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

የጁቤ እና መካኒሳ የባንኩ ሥራ አስፈፃሚዎች እና የአካባቢዎቹ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቀው ተከፍተዋል ፡፡

ቅርንጫፎቹ ተመርቀዉ ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከባንኩ የኮር ባንኪንግ ሥርዓት ጋር በኔትወርክ የተሳሰሩ ሲሆን፣ ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከተለመደው በተለየ መልኩ ረዘም ላሉ የሥራ ሰዓታት ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዓባይ ባንክ ደንበኞቹን ያሉበት ድረስ ቀርቦ ለማገልገል በማለም በቅርቡ ቅርንጫፎቹን በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች እንደሚያስፋፋ ሲገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ዓባይ – ታማኝ አገልጋይ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.