ዓባይ ባንክ 271ኛ ቅርንጫፉን ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጥ 6ኛ ቅርንጫፉን ከፈተ

ዓባይ ባንክ 271ኛ ቅርንጫፉን ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጥ 6ኛ ቅርንጫፉን ከፈተ

ዓባይ ባንክ 271 ቅርንጫፉን በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ  ስልጤ ሰፈር አደባባይ ወደ አለም ባንክ መሄጃ ላይ “አለም ባንክ አማና ከወለድ ነጸ ቅርንጫፍ” በሚል ስያሜ መጋቢት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

ቅርንጫፉ የባንኩ ሥራ አስፈፃሚዎች እና የየአካባቢዎቹ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቀው ተከፍተዋል ፡፡

ቅርንጫፉ ተመርቆ ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ከባንኩ የኮር ባንኪንግ ሥርዓት ጋር በኔትወርክ የተሳሰሩ ሲሆን፣ ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከተለመደው በተለየ መልኩ ረዘም ላሉ የሥራ ሰዓታት ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ዓባይ ባንክ ደንበኞቹን ያሉበት ድረስ ቀርቦ ለማገልገል በማለም በቅርቡ ቅርንጫፎቹን በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች እንደሚያስፋፋ ሲገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ዓባይ – ታማኝ አገልጋይ!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.